Amharic Bible

መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።
Chapter 1 of 29
left-arrow Chapter - 1 right-arrow
Verse 1

[see v2]

Verse 2

አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥ ቃይናን፥ መላልኤል፥

Verse 3

ያሬድ፥ ሄኖክ፥ ማቱሳላ፥ ላሜሕ፥

Verse 4

ኖኅ፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት።

Verse 5

የያፌት ልጆች፤ ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥

Verse 6

ያዋን፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ።

Verse 7

የጋሜርም ልጆች፤ አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ። የያዋንም ልጆች፤ ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ።

Verse 8

የካምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን።

Verse 9

የኩሽም ልጆች፤ ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰብቃታ። የራዕማም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን።

Verse 10

ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ኃያል መሆንን ጀመረ።

Verse 11

ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥

Verse 12

ነፍተሂምን፥ ፈትሩሲምን፥ ፍልስጥኤማውያን የወጡበትን ከስሉሂምን፥ ከፍቶሪምን ወለደ።

Verse 13

ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥

Verse 14

ኬጢን፥ ኢያቡሳዊውን፥ አሞራዊውን፥

Verse 15

ጌርጌሳዊውን፥ ኤዊያዊውን፥ ዐርካዊውን፥

Verse 16

ሲኒያዊውን፥ አራዴዎንን፥ ሰማሪዎንን፥ አማቲን ወለደ።

Verse 17

የሴምም ልጆች፤ ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሳሕ።

Verse 18

አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ።

Verse 19

ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ በዘመኑ ምድር ተከፍላለችና የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነበረ።

Verse 20

ዮቅጣንም አልሞዳድን፥

Verse 21

ሣሌፍን፥ ሐስረሞትን፥ ያራሕን፥ ሀዶራምን፥

Verse 22

አውዛልን፥ ደቅላን፥ ዖባልን፥ አቢማኤልን፥

Verse 23

ሳባን፥ ኦፊርን፥ ኤውላጥን፥ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ።

Verse 24

፤

Verse 25

ሴም፥ አርፋክስድ፥ ሳላ፥ ዔቦር፥ ፋሌቅ፥

Verse 26

፤

Verse 27

ራግው፥ ሴሮሕ፥ ናኮር፥ ታራ፥ አብርሃም የተባለ አብራም።

Verse 28

የአብርሃምም ልጆች፤ ይስሐቅ፥ እስማኤል።

Verse 29

ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው። የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፤ ከዚህ በኋላ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥ መብሳም፥

Verse 30

ማስማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥

Verse 31

ኢጡር፥ ናፌስ፥ ቄድማ፤ እነዚህ የእስማኤል ልጆች ናቸው።

Verse 32

የአብርሃምም ገረድ የኬጡራ ልጆች፤ ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳን፥ ምድያም፥ የስቦቅ፥ ስዌሕ። የዮቅሳንም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን።

Verse 33

የምድያምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ።

Verse 34

አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅም ልጆች ዔሳውና እስራኤል ነበሩ።

Verse 35

የዔሳው ልጆች፤ ኤልፋዝ፥ ራጉኤል፥ የዑስ፥ የዕላም፥ ቆሬ።

Verse 36

የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ፥ ቲምናዕ፥ አማሌቅ።

Verse 37

የራጉኤል ልጆች፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ።

Verse 38

የሴይርም ልጆች፤ ሎጣን፥ ሦባል፥ ጽብዖን፥ ዓና፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን።

Verse 39

የሎጣንም ልጆች፤ ሖሪ፥ ሔማም፤ ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።

Verse 40

የሦባል ልጆች፤ ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥ አውናም። የጽብዖንም ልጆች፤ አያ፥ ዓና።

Verse 41

የዓና ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶንም ልጆች፤ ሔምዳን፥ ኤስባን፥ ይትራን፥ ክራን።

Verse 42

የኤጽር ልጆች፤ ቢልሐን፥ ዛዕዋን፥ ዓቃን። የዲሳን ልጆች፤ ዑፅ፥ አራን።

Verse 43

በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማይቱም ስም ዲንሃባ ነበረ።

Verse 44

ባላቅም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የባሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።

Verse 45

ኢዮባብም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የቴማን አገር ሰው ሑሳም ነገሠ።

Verse 46

ሑሳምም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ በሞዓብ ሜዳ ምድያምን የመታው የባዳድ ልጅ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ዓዊት ነበረ።

Verse 47

ሃዳድም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የመሥሬቃ ሰው ሠምላ ነገሠ።

Verse 48

ሠምላም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ በወንዙ አጠገብ ያለችው የረሆቦት ሰው ሳኡል ነገሠ።

Verse 49

ሳኡልም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ነገሠ።

Verse 50

በኣልሐናንም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ፋዑ ነበረ፤ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች፤ ሃዳድም ሞተ።

Verse 51

የኤዶምያስም አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥

Verse 52

አህሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፊኖን አለቃ፥

Verse 53

ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ ሚብሳር አለቃ፥

Verse 54

መግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፤ እነዚህ የኤዶምያስ አለቆች ነበሩ።

Chapter -
1